✦
Auto Fetched
•Zemarian Collection
ሃያሉ ሚካኤል
ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረጻድቅLyrics
♡ ኃያሉ ሚካኤል ♡
ኃያሉ ሚካኤል ምድርን ይሸፍናል
ደመናትን ጋርዶ ጥላ ይሆነኛል
ሚካኤል ይላካል ፍጥረት እንዲጽናና
የላከው እግዚአብሔር ደግ አምላክ ነውና
የዱራታየስ ክብር የሶስና ረዳት
ያሳደከኝ መልአክ ሚካኤል የኔ አባት
በጨነቀኝ ጊዜ ስታመን በምልጃህ
ትደርስልኛለህ ከዐይን ጥቅሻ ፈጥነህ
በመንገዴ ሁሉ ደመና ዘርግተህ
አይዞሽ ልጄ በለኝ ባርከኝ በመስቀልህ
ርኅሩህ ሚካኤል መንገዴን አደራ
ጠብቀኝ ልጅህን ከክፉ መከራ
ሲኦል እንዳይበላኝ በክፉ ስራዬ
የ መላእክት አለቃ ዋሴ ጠበቃዬ
ለንሰሐ አብቃኝ ልቤን አስተካክለው
የሞተ ደብዳቤ ዬን እንደ ባሕራን ሻረው
በቤተ መቅደሱ አሳድገኸኛል
የከበረ ስምህ በልቤ ታትሟል
ስምህን ደጋግሜ ሚካኤል እላለሁ
በሄድኩበት ሁሉ እመሰክራለሁ
በሄድኩበት ሁሉ እዘምርልሃለሁ
ዘማሪት ሊዲያ ታደሰ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.