Auto Fetched
•Zemarian Collection
መስቀል ክብሬ ነው
ዘማሪ አቤል መክብብ✞ መስቀል ክብሬ ነው ✞
ምልክቴ ነው ከገጽ ማምለጫዬ
መስቀል ክብሬ ነው ከክፉ መውጫዬ [፪]
የእባቡ እራስ ሚቀጠቀጥበት
በመስቀል ቤዛነት መርገም ተሻረበት
ሰው በዕፀ መስቀል ከእግዚአብሔር ታረቀ
የምሕረት ቀን ወጣ መከራው ራቀ
ኦ በመስቀል ጠላት ተቸገረ
ኦ በመስቀል ጨለማው ተሻረ
ኦ በመስቀል ደሙን አፈሰሰ
ኦ በመስቀል ስጋውን ቆረሰ
ፊቴን ሰውነቴን በእርሱ አማትባለው
በልቤ አትሜ በአንገቴ አስረዋለው
አይሁድ በሚክዱት እኔ ግን አምኜ
እግሩ ለቆመበት እሰግዳለሁ ድኜ
ኦ በመስቀል እስረኛ ተፈታ
ኦ በመስቀል ከሳሹ ተረታ
ኦ በመስቀል ሞትን ገደለልን
ኦ በመስቀል በሩን ከፈተልን
የቤዛ ክርስቶስ የክብሩ ዙፋን ነው
በዕምነት የሚያጸና በስሙ ላመነው
የቅድስና የሕይወት ማኅተም
መስቀል ትምክህት ነው እስከ ዘለዓለም
ኦ በመስቀል ፍቅሩን ገለጸልን
ኦ በመስቀል ነብሱን ለኛ ሰጠን
ኦ በመስቀል እንባችን ታበሰ
ኦ በመስቀል ጸጋ ተለበሰ
ፊቴን ሰውነቴን በእርሱ አማትባለው
በልቤ አትሜ በአንገቴ አስረዋለው
አይሁድ በሚክዱት እኔ ግን አምኜ
እግሩ ለቆመበት እሰግዳለሁ ድኜ
ኦ በመስቀል እስረኛ ተፈታ
ኦ በመስቀል ከሳሹ ተረታ
ኦ በመስቀል ሞትን ገደለልን
ኦ በመስቀል በሩን ከፈተልን
መዝሙር
ዘማሪ አቤል መክብብ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.