✦

Auto Fetched

•

Zemarian Collection

ማር ሚካኤል

ዲ/ን አዝማሪያም
Lyrics

♡ ማር ሚካኤል ♡

ማር ሚካኤል ልበል

ማር ሚካኤል ልበልህ

ባርከህ ያሳደከኝ በቅኔ በዜማ

መዝሙር አልሰስትም አባቴ ላንተማ

ጅማሬዬ ታናሽ ያልበቃሁ ብሆንም

እንድጸና አውቃለሁ ከፊቴ ስትቀድም

ፍጻሜዬ እንዲያምር እንዲዋብ በቤትህ

አበርታኝ ልበርታ አጽናኝ ልጽና ልጅህ

ባህሩን ክፈለው በደረቅ እንዳልፈው

እንዳልፈራ አበርታኝ እጄን በእጅህ ያዘው

ከእንቅልፍ ያነቃኛል የደጅህ ደወል

በሌሊት መጥቼ ቤትህ እንድውል

በሄድኩበት ሁሉ ካፌ አትነጠልም

የማር ወለላ ነው ሚካኤል ያንተ ስም

ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለ አፌ

መውደድህ እውነት ነው በምልጃህ ተርፌ

በሞቱ ቀጠሮ ሠርግ የደገስክለት

ምን አለ ባሕራን ስታተርፈው ከሞት

ዛሬም ታምርህን ትድግናህን አይተው

ብዙዎች ይልሀል ሚካኤል ሙት አንሳው

ረዳኤ ምንዱባን በስደት ደጋፊ

ከክፉ ከልለህ በድል አሳላፊ

አለቱን ከፍለህው በበትረ መስቀል

ከጭንጫው ሰጠህን ማርና ጸበል

ቀድሞ ለእስራኤል ያኔ እንዳደረከው

ያኔ የሰማነውን ዛሬ ሆኖ አየነው

የብርሀኑን አምድ ፋና ተከትለን

ከቅዱሳን ስፍራ ዛጅርማኤል ደርሰን

ከእንቅልፍ ያነቃኛል የደጅህ ደወል

በሌሊት መጥቼ ቤትህ እንድውል

በሄድኩበት ሁሉ ካፌ አትነጠልም

የማር ወለላ ነው ሚካኤል ያንተ ስም

ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለ አፌ

ውልድህ እውነት ነው በምልጃህ ተርፌ

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening